ሰኞ 16 ሜይ 2016



                    የራሷ ኣሮባት የሌላውን ታማስላለች 

          ሁሉም የኣፍሪካ ሃገራት በባርነት ቀኝ ግዛት ሲገዙ በዛን ግዜ ግን ሁለት ሃገራት ነፃነታቸውን ኣስጠብቀዉ ነበር። ሃገራቸው ለባዕድ አሳልፈው ካልሰጡት ሃገሮች መካከል ኣንድዋን ኢትዮጵያ ሃገራችን ነበረች፡፡ ሃገራችን ለባዕድ ኣሳልፈን ኣንሰጥም ኣንገዛም በማለት ስንት ኣያቶቻችን ለነፃነታቸው ተዋግተዋል ሙተዋል ቆስለዋልም ። ይሄ ሁሉ ያደረጉት ሃገራቸው በፈረንጅ እንዳትገዛ በለው ነው ።

       ግና የአሁኑ ትዉልድ ከእሳቸው ዘር የወጣ አይመስልም ፡፡ፈሪ በራሱ ማንነት የማይኮራ በዓለም ዉስጥ ልዪ መሆኑን የማያውቅ ስለ ራሱን ትቶ ሰለ ሌላ ዓለም የሚያወራ የራሱ የሆኑት ድንቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት መሆኑን የራሱ የሆነ የፊደል ቀለም እና ቁጥር ያለው መሆኑን እያወቀ ኣንድን ነገር ለማድረግ ሲያስቡ ግን የራሷን አሮባት የሌላውን ታማስላለች እንደሚባለው የራሳቸውን ቁጭ አድርገው የሌላውን ቋንቋ ይጠቀማሉ ።

       ለምሳሌ ያክል እንኻን ብንጠቅስ ስፓ ፣ናይስ ፣ መርሲ ፣የስ ፣ብሉ ሌሎችም ኣሉ ። እነዚህ የተጣሩ ውሃ ናቸው ፡፡ በእነዚህ የታሸጉ ውሃዎች በያንዳንዱ የውሃ ኻዳ ላይ ከታች የተፈጥሮ ምንጭ ውሃ የሚል ፅሁፍ ኣላቸው ፡፡ ችግሩ ስናይ የተፈጥሮ ምንጭ ውሃ እያሉ የሚሰሩት በዛው ኣካባቢ እያለ የሚሰየሙት ወይም የሚሰጣቸው ስም ግን የኢንግሊዘኛ ቋንቋ ነው ። በዚህም መልኩ ነው ሳይታወቀን በባርነትና እየተገዛነው ያለነውን ።

     እነኚህ ችግሮች ይዘን የተፈጥሮ ፣ያገራችን ፣ የራሳችን ምናምን እያልን እናስታውቃለን ።እነዚህ ነገሮች የተሰጣቸውን ስያሜ ብናስተካክለው ማለትም ሀገርኛ የሆነ ስያሜ ብንሰጣቸው ጥሩ ይመስለኛል ።ለምሳሌ ማይሎሚ  ፣ ምሕረት ፣ ፀበል ውሀና ሌሎችም እያልን መሰየም እንችላለን ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ