ሰኞ 16 ሜይ 2016




                          ከ ላክስ ምን ተገነዘቡ!


          ኣንድ ማስታወቂያ ስንሰራ የራሱ የሆነ መንገድ እና አካሄድ ኣለው :: የምንሰራው ማስታወቂያ መቼና እንዴትለማንስ ነዉ የምናስተላልፈው ማንስ ነዉ የሚመለከተው ብለን በደምብ ማሰብ ያለብን ይመስለኛል ፡፡ ምክንያቱም ኣንድ ማስታወቂያ ተሰርቶ ተመልካች ላይ ሲቀርብ ብዙ ተመልካች ነዉ ያለዉ ፡፡ ማለትም ከኣዋቂ ጀምሮ እስከ ህፃን ጽረስ ፡፡

         በዚህም የተነሳ ስለ ላክስ የገላ ሳሙና የተሰራውን ማስታወቂያ ስንመለከት፡፡ ችግሩ የዚህን ማስታወቂያ ለማስተዋወቅ የተጠቀመበትን ነገር ላክስ የገላ ሳሙና ለፍቅረኛሞች ብቻ እንዲጠቀሙበት ተብሎ የተሰራ ነዉ የሚመስለው ፡፡ ማስታወቅያዉ ስንመለከተው ላክስ ሳሙና ወንዶች ለማማለል እና በመኣዛዉ የሚመሰጥበት አይነት ነገር ነዉ ያለውን ፡፡ ባጠቃላይ የላክስ ሳሙና ማስታወቂያ ስሜት ቀሽቃሽ እና ለወሲብ የሚጋብዝ ኣይነት ማስታወቂያ ነው የተሰራው የሚል ሀሳብ ነው ያለኝ፡፡

        የዚህ የላክስ የገላ ሳሙና  ማስታወቂያ ከዚህ በተሻለ መንገድ መቅረብ ይችል ነበር እላለሁ፡፡
ለምሳሌ ያክል ፊታቸው ወይም ደግሞ ገላቸውን በላክስ ሳሙና እየታጠቡ ቢሆን ከዛ በመቀጠል ሳሙናው በቆዳቸው ላይ ያመጣውን ለውጥ በምስል ወይም በቃል በመናገር የማስታወቂያዉ መልእክት ማስተላለፍ ይችሉ ነበር ፡፡

        ባጠቃላይ ላክስ የገላ ሳሙና ላይ የተሰራው ማስታወቂያ በዚህ መልክ ለማየት ሞክሬያለሁ ፡፡ ኣንድን ማስታወቂያ ስንሰራ ለየት እንዲል ተብሎ ባልሆነ መልኩ ተሰርቶ መቅረብ የለበትም ፡፡ የምንሰራው ነገር ሁሉንም ሰዉ የሚያካትት መሆን እንዳለበት እና ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆን ያለበት ይመስለኛል ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ